ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
BBC News, አማርኛ - ዜና
ዜና
ኤርትራ "በሌሎች ኃይሎች ተማምና በጥፋት መንገድ የምትቀጥል ከሆነ ከባድ ውጤት እንደሚኖረው" ጠ/ሚ ዐቢይ አስጠነቀቁ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ሰላም እንደምትፈልግ እና የልማት አጋር መሆን እንደምትሻ ጠቅሰው፤ ኤርትራ "በሌሎች ኃይሎች ተማምና በጥፋት መንገድ የምትቀጥል ከሆነ ግን ከባድ ውጤት እንደሚኖረው" ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰኞ ጥቅምት 9/2013 ዓ. ም. በትግርኛ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ ነው ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር አጋርነት እንደምትፈልግ ተናግረው የማስጠንቀቂያ መልዕክትም ያስተላለፉት።
ቀጥታ, የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር በእስራኤል ባደረጉት ይፋዊ ያልሆነ ጉብኝት ከኔታንያሁ ጋር መገናኘታቸው ተዘገበ
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግዜት ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር መገናኘታቸውን አክሲዮስ ዘገበ። የአሜሪካው የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን አክሲዮስ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሁለት ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ሄግዜት ወደ እስራኤል ይፋ ያልተደረገ ጉብኝት አድርገዋል።
የትግራይ ባለአደራ አስተዳደር አምስቱ ተሿሚዎች እነማን ናቸው?
መስከረም አጋማሽ ላይ ዳግም ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ አብዛኛው የትግራይ ክልል አካባቢ በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት እና በአጋር ኃይሉ ቁጥጥር ስር ገብቷል። ክልሉን በማረጋጋት እና መልሶ በመገንባት በምርጫ የሚመጣ አስተደዳር ቦታውን አስኪረከብ ድረስ ለስድስት ወራት የሚቆይ የባለአደራ አስተዳደር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተሹሟል። አምስት አባላት ያሉት ይህ ባለአደራ አስተዳደርን የሚመሩት እና የመቀለ ከተማ ከንቲባ እንዲሆኑ የተሰየሙት አምስቱ ሰዎች እነማን ናቸው?
ህወሓትን "ተገንጣይ" ያሉት ሩቢዮ በአዲስ አበባ የድሮን ጥቃት ተፈፅሞ እንደነበር ተናገሩ
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ላለፉት ሦስት ሳምንታት ከፌደራል መንግሥቱ እና ከአጋሮቹ ጋር እየተዋጋ የሚገኘውን ህወሓት "ተገንጣይ ቡድን" በማለት በአዲስ አበባ የድሮን ጥቃት ተፈጽሞ እንደነበር ተናገሩ። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ያለው ውጥረት እየጨመረ በመምጣቱ ያላቸውን ስጋትም ገልጸዋል።
የመንግሥት ለውጥ - የሰሜኑ ጦርነት - የፓርላማ የምሬት ንግግር - ስደት ፡ የገዱ አንዳርጋቸው የለውጡ ስምንት ዓመታት
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአገር ከመውጣታቸው በፊት መስከረም ማብቂያ ላይ በአዲስ ምክር ቤት የተተካው የቀድሞው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል፣ በክልል እና በፌደራል መንግሥቱ ውስጥ ከፍተኛ ባለሥልጣን ነበሩ። ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን የመጡበት ለውጥ ውስጥ ሚና ከነበራቸው ሰዎች መካከልም አንዱ ነበሩ፤ አሁን ግን በስደት ላይ ይገኛሉ። አቶ ገዱ ባለፉት 8 ዓመታት ያለፉባቸውን ውጣ ውረዶች በተመለከተ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
ቢቢሲ አማርኛ በቲክቶክ
አስተማማኝ ዜና እና መረጃን ቅድሚያ ለማግኘት ቢቢሲ አማርኛን ቲክቶክ ላይ ይከተሉ
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናልን ይቀላቀሉ
የሰሜን ኢትዮጵያ ቀውስ
የፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ክልል ጦርነቱ መጠናቀቁን ገልጾ የባለአደራ አስተዳደር መመሥረቱን አስታወቀ
በትግራይ ክልል ለስድስት ወራት የሚቆይ ባለ አደራ አስተዳደር ተቋቋመ። በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተቋቋመው ይህ ባለአደራ አስተዳደር በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ነጻና ግልጽ ምርጫ በማከናወን ትግራይ የፌዴሬሽኑ አካል የምትሆንበትን ሁኔታ የማመቻቸት ኃላፊነት ተሰጥቶታል። በአስተዳደሩ ውስጥ በዋና አስፈጻሚነት ከተካተቱት መካከል የትግራይ ሰላም ኃይልን የሚመሩት ብ/ጄ ገብረ እግዚአብሔር በየነ ይገኙበታል።
ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጋር በተያያዘ ባለፉት 5 ወራት አሜሪካ የወሰደቻቸው 5 እርምጃዎች
ደም አፋሳሹ የትግራይ ጦርነት በፕሪቶሪያ ስምምነት አማካኝነት እንዲገታ ከፍተኛ ሚና ከነበራቸው አካላት መካከል የአፍሪካ ኅብረት እና አሜሪካ ይጠቀሳሉ። አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ ዋነኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ምዕራባውያን አገራት አንዷ ናት። የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከሳምንታት በፊት ዳግም ሲቀሰቀስ ቀድመው መግለጫ ካወጡ አገራትም አንዷ ናት። አሜሪካ ከጦርነት መነሳት በፊት እና በኋላ የወሰደቻቸውን እርምጃዎች እንደሚከተለው ቃኝተናል።
ሶማሊላንድ በግብፅ የተመሠረተውን ጥምረት በመቃወም ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትቆም ገለጸች
ሶማሊላንድ የኢትዮጵያን ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥል የትኛውንም ዓይነት ጣልቃ ገብነት እና ጥምረትን እንደምትቃወም ገለጸች። ነጻ አገርነቷን ያወጀችው ሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ ከጎረቤታቸው ኢትዮጵያ ጋር ባላቸው ትብብር ከፍተኛ መተማመን እንዳላቸው ገልጸው "የኢትዮጵያን መረጋጋት እና ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥል የትኛውንም ጣልቃ ገብነት እንቃወማለን" ብለዋል።
'በሕይወት እንተርፋለን አላልንም' ፡ በህወሓት ቁጥጥር ስር የቆዩት የቀድሞ ባለሥልጣናት ምን ገጠማቸው?
የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደን ጨምሮ፣ አራት የቀድሞ ባለሥልጣናት ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ በህወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር ከነበሩበት እስር አምልጠው በኢትዮጵያ ሠራዊት እጅ ከገቡ በኋላ ወደ መቀለ መመለሳቸውን ተናግረዋል። ባለሥልጣናቱ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በቀድሞ ጓዶቻቸው ከየቤታቸው ታግተው ከተወሰዱ በኋላ ያሳለፉትን እና እንዴት ሊያመልጡ እንደቻሉ ከመካከላቸው አንዱ ለቢቢሲ አጋርተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሩቢዮ ምን ተነጋገሩ?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር በስልክ ተወያይተዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ፤ ንግግራቸው ከኤርትራ ጋር "እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት" የተመለከተ መሆኑ ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የውይይቱን ይዘት በዝርዝር ባይገልጹም "እጅግ ፍሬያማ" መሆኑን አስታውቀዋል።
ሶማሊያ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል በተፈጠረው ውጥረት ገለልተኛ መሆኗን ገለፀች
የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ሐሰን ሞሐመድ አሊ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል በተፈጠረው ውጥረት አገራቸው "ገለልተኛ" መሆኗን ተናገሩ። ምክትል ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ከቢቢሲ ሶማልኛ ጋር እሁድ ጥቅምት 1/2019 ዓ.ም. በነበራቸው ቃለ ምልልስ ወቅት ነው።"የሶማሊያ መንግሥት አቋም ሰላማዊ እና ገለልተኛ ነው" ያሉት ሚኒስትሩ ከአገራቱ ጋር ታሪካዊ፣ መልክዓ ምድራዊ እንዲሁም ሃይማኖታዊ ትስስር እንዳለ ተናግረዋል።
ወደ ትግራይ የተጓዙት የፌደራል መንግሥቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ምን አሉ?
በትግራይ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ተቋርጦ የነበረው የአውሮፕላን በረራ በትናንትናው ዕለት ሲጀመር የፌደራል መንግሥቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ወደ መቀለ እና አዲግራት በማምራት ነዋሪዎችን ማግኘታቸውን ገልጸዋል። አቶ ጌታቸው ረዳ ከ18 ወራት በኋላ ወደ ክልሉ ዋና መዲና መመለሳቸውን ሲናገሩ፣ ዶ/ር አብርሃም በላይ ደግሞ "ሰላም የተጠማው ሕዝባችንን ጎበኘነው” ብለዋል። የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው በመቀለ እና አዲግራት በነበራቸው ቆይታ "ጥልቅ የሰላም ጥማት" ማየታቸውን ገልጸዋል።
ስለ ሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት መንግሥት ለምን ዝምታን መረጠ? የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ?
በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት ሁለት ሳምንት አልፎታል፤ የፌደራሉ መንግሥት እና አጋር ኃይሉ መቀለን እና ሌሎች የትግራይ አካባቢዎችን ተቆጣጥረዋል። ከጦርነቱ ጅማሮ አንስቶ ተሳታፊ እንደሆኑ ሲነገር የነበረው የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው በብዛት ወደ ትግራይ መግባታቸው ተዘግቧል። ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ ባድረጉት ንግግርም ሆነ መንግሥታቸው ስለ ጦርነቱ እስካሁን በይፋ ያሉት ያሉት ነገር የለም፤ ለምን?
ስለ ሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከዲፕሎማሲ ውዝግብ እስከ ፀጥታው ምክር ቤት አቤቱታ እስካሁን የምናውቀው
ሁለት ሳምንት ያለፈው በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ጦርነት እንደቀጠለ ነው። በዚህ ሳምንት የጦርነቱ ዋነኛው ጉዳይ የኤርትራ ወታደሮች ከድንበር በሻገር በብዙ ኪሎ ሜትሮች ርቀው ወደ ኢትዮጵያ ግዛት መግባታቸው ነው። ይህም ኢትዮጵያ ወረራ እንደተፈጸመባት በመግለጽ ለመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት ደብዳቤ እንድትጽፍ አድርጓታል። እስካሁን በተፈጠረው ቀውስ ዙሪያ ስላሉ ዋና ዋና ሁኔታዎች ምን እናውቃለን?
ትግራይ በኮማንድ ፖስት እንደምትመራ እና ከስድስት ወር በኋላ ምርጫ እንደሚካሄድ ተነገረ
የህወሓት መሪዎች መቀለን ጨምሮ ከበርካታ የትግራይ ከተሞች ለቅቀው ከወጡ በኋላ ክልሉ በፌደራል መንግሥቱ ኮማንድ ፖስት ሥር እንደሚቆይ እና በትግራይ ምርጫ እንደሚካሄድ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ። የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት እና በአሁኑ ጊዜ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ይህንን የተናገሩት ቲቢኤስ ከተባለ መገናኛ ብዙኃን ጋር በትግርኛ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው።
የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?
የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቪድዮዎች
ቪዲዮ, “እኛ አዲስ አገር ስለሆንን ምርጫ ለማካሄድ ዝግጁ አይደለንም”
ለጋዜጠኞች ክፍት ወዳልሆነችው ኤርትራ በቅርቡ የመጓዝ ዕድል አግኝታ የነበረችው የሮይተርስ ዘጋቢ ጁሊያን ፓራቪሲኒ አሥመራ በጣሊያን ጊዜ የተገነቡ ሕንጻዎቿን ጠብቃ ብዙም እንቅስቃሴ የማይደረግባት ሆና አግኝታታለች። የኢንተርኔት አገልግሎት ቁጥጥር የሚደረግበት እና ውስን በመሆኑ ሕዝቡ ከቀሪው ዓለም መነጠሉንም ታዝባለች። የአገሪቱ ባለሥልጣናትም ኤርትራ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጁ አይደለችም ብለዋታል።
ቪዲዮ, የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እና ከኤርትራ ጋር ያለው ውጥረት
በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ቀውስ የበለጠ ያወሳስባል ስለተባለው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እስካሁን ምን እናውቃለን? ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በቀጥታ ጦርነት ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ?
ቪዲዮ, “ከትብብሩ ጀርባ ኤርትራ፣ ግብፅ እና ሱዳን አሉበት” ጃዋር መሐመድ
ሰባት የተቃዋሚ ኃይሎች የፈጠሩትን ትብብር አስመልክቶ ቢቢሲ ከፖለቲከኛው ጃዋር መሐመድ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጓል። በቃለ መጠይቁ ትብብሩ ሦስት ውጤቶች ሊኖሩት እንደሚችሉ ተናግረዋል። ከዚህም ባለፈ ኤርትራ፣ ግብፅ እና ሱዳን ከትበብሩ ጀርባ እንዳሉ ተናግረዋል።
ቪዲዮ, ሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ሊያጠፋን ይችላል?
ሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) በተለያዩ ዘርፎች ላይ ውሎ ከፍተኛ ጥቅምን አስገኝቷል። በዚህም ውስብስብ ነገሮችን ከማቅለል አልፎ በርካታ ተግባራትን በቀላሉ ለመፈጸም አስችሏል። ይህ ደግሞ በተለያዩ መስኮች የሰዎችን ሥራ እየወሰደ እንደሆነ ሲገልጽ ቆይቶ አሁን ደግሞ የሰውን ልጅ ሊያጠፋ ይችላል የሚል ስጋት እየተሰማ ነው
ቪዲዮ, አነጋጋሪ የሆነው የቻይናው ፕሬዝዳንት የካይሮ ጉብኝት
የቻይናው ፕሬዝዳንት ካይሮን በጎበኙበት ወቅት ግብፅ በአባይ እና በቀይ ባሕር ላይ የምታራምዳቸውን አቋሞች የሚደግፍ የጋራ መግለጫ ሁለቱ አገራት አውጥተዋል። የዓለማችን አንዷ ኃያል አገር ቻይና ይህንን አቋም ማንጸባረቋ ለኢትዮጵያ ምን ማለት ነው?
ቪዲዮ, ግብፅ ትቀላቀለዋለች እየተባለ ያለው ቱርክ፣ ሳዑዲ እና ፓኪስታን የመሠረቱት 'የሙስሊም ኔቶ'
ቱርክ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ፓኪስታን 'የመካ ስምምነት'ን ከፈረሙ ከአንድ ሳምንት በላይ ሆኗቸዋል። አንዳንድ ተንታኞች አገራቱ የተፈራረሙትን የመከላከያ ስምምነት "የሱኒ ስምምነት" ወይም "የሙስሊም ኔቶ" ሲሉ ጠርተውታል። አንዳንዶች እንደ ኢራን እና እስራኤል ላሉ አገራት የተላለፈ መልዕክት አድርገው አቅርበውታል። ሌሎች ደግሞ ይህ ስምምነት አገራቱ ለደኅንነት ዋስትና በዩናይትድ ስቴትስ ላይ ያላቸውን ጥገኝነት ለመቀነስ ያላቸውን ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ነው ይላሉ። ነገር ግን ሙሉው ስምምነት ለሕዝብ ይፋ ባለመሆኑ እየተሰሙ ያሉት መላምቶች ብቻ ናቸው።
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
አነጋጋሪ ጉዳይ
ኢትዮጵያ አዲስ ከገነባችው የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ ምን ያህል ታተርፋለች?
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከሚጠቀሱ የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካዎች አንዱ ሊሆን ይችላል የተባለ ማጣሪያ ሥራ አስጀምራለች። ይህ ተቋም በጥሬው ወደ ሌሎች አገራት የሚላከውን የአገሪቱን ከፍተኛ መጠን ያለውን ወርቅ በማጣራት ዕሴት ጨምሮ ከፍተኛ ገቢን እንደሚያስገኝ እየተነገረ ነው። የፋብሪካው ከፍተኛ ባለድርሻ የሆነው መንግሥታዊው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ለቢቢሲ ኒውስ ዴይ ፕሮግራም ስለ ፋብሪካው ተናግረዋል።
"ሁለት እህቶቼን አጥቻለሁ"፡ 139 ሰዎች ከሞቱበት የጂቡቲው የጀልባ አደጋ የተረፉ ኢትዮጵያውያን ምስክርነት
ከጂቡቲ ወደ የመን እየተጓዘ የነበረ ጀልባ ተገልብጦ 80 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከአደጋው መትረፋቸውን ዓለም አቀፉ የስደኞች ተቋም (አይኦኤም) ገልጿል። ለመስከረም 29 አጥቢያ ማለትም መስከረም 28/2019 ዓ. ም. ምሽት ላይ ከጂቡቲ የወደብ ከተማ ኦባክ በስተሰሜን በምትገኘው ጉህሬ አቅራቢያ ጀልባው ተገልብጦ 139 ሰዎች ሞተዋል። ከዚህ አሰቃቂ አደጋ የተረፉ ኢትዮጵያውያን አደጋው እንዴት እንደተከሰተ እና የገጠማቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታሪክ፣ አሠራር እና አወቃቀር
ባለፈው ዓመት በተካሄደው ምርጫ መሠረት አዲሱ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ መስከረም 25/2019 ዓ.ም. ሥራውን ይጀምራል። ባለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት በአገሪቱ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ የሚያሳልፈው ምክር ቤት ታሪክ ምን ይመስላል? የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አወቃቀር እና ሥራውን እንዴት እንደሚያከናውን ምን ያህል ያውቃሉ?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዓመት ከ600 ቶን በላይ የከበሩ ማዕድናትን የማጣራት አቅም ያለው ፋብሪካ ሥራ ማስጀመራቸውን ተናገሩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዓመት ከ600 ቶን በላይ የከበሩ ማዕድናትን የማጣራት አቅም ያለው ፋብሪካ ሥራ አስጀመሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቅዳሜ መስከረም 30/2019 ዓ.ም. ሥራ ያስጀመሩት ይህ የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ እስካሁን ድረስ ጥሬ ወርቅን ወደ ውጭ በመላክ ላይ ብቻ ተወስና ለቆየችው ኢትዮጵያ በዘርፉ ላይ ያለውን የእሴት መጨመር ችግር እንደሚቀርፈው ተናግረዋል። የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካው በአገር ውስጥ እና በቀጣናው የሚመረተው ወርቅ እሴት ታክሎበት በተሻለ ዋጋ ለገበያ ለማቅረብ ከፍተኛ አቅም እንደሚፈጥርም ጨምረው አብራርተዋል።
ትብብር የመሠረቱት ታጣቂ ቡድኖች አንድ የሚያደርጋቸው እና የሚያለያያቸው ምንድን ነው?
ሰባት ታጣቂ ቡድኖች "ትብብር ለኅልውና" የተሰኘ ጥምረት መመሥረታቸውን እሁድ መስከረም 10/2019 ዓ.ም. አስታውቀዋል። ይህንን ትብብር ከመሠረቱት የትጥቅ ቡድኖች መካከል የተወሰኑት በአንድ ወቅት በጠላትነት የሚተያዩ እና እርስ በርስ የተዋጉ ነበሩ። እነዚህ ትብብር መሥርተናል የሚሉት ታጣቂ ቡድኖች ባለፉት ዓመታት በጠላትነት የሚተያዩ አንዳንድ ጊዜም ግጭት ውስጥ የገቡ ነበሩ። ቡድኖቹን ምን አንድ ያደርጋቸዋል? በምንስ ይለያያሉ?
በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ስለተቀሰቀሰው ግጭት እስካሁን የምናውቀው
የትግራይ የእርስ በርስ ጦርነት በፕሪቶርያ ስምምነት ከተገታ ወዲህ ከረቡዕ መስከረም 13 አንስቶ ግጭት በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግመኛ ተቀስቅሷል። ረቡዕ ዕለት ግጭቱ ስለ መጀመሩ ይፋዊ መረጃ ቢወጣም ማክሰኞ ዕለት በትግራይ አላማጣ ከተማ ተከታታይ የድሮን እና የአውሮፕላን ጥቃቶች መፈጸማቸው ተዘግቧል። ግጭቱ ይፋ መሆኑን ተከትሎ የተለያዩ ወገኖች አቋማቸውን እያንጸባረቁ ነው። ስለ ግጭቱ አስካሁን የምናውቀው ምንድን ነው?
ከየፈርጁ
በአዲስ አበባ ተማሪዎችን ከፍተኛ ክፍያ ከሚጠይቁት ትምህርት ቤቶች መካከል ሦስቱ
በአዲስ አበባ የሚገኙ አንዳንድ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች ለአንድ ተማሪ በዓመት ከሚያስከፍሉት ክፍያ አንጻር ከፍተኛ የሚባሉ ዋጋዎችን ያስቀምጣሉ። በአውሮፓውያኑ 2026/27 የትምህርት ዘመን የወጡ የክፍያ መረጃዎች እነዚህ ትምህርት ቤቶች በዓመት እስከ 37 ሺህ ዶላር በላይ ወይም ወደ ስድስት ሚሊዮን የሚጠጋ ብር እንደሚያስከፍሉ ያመለክታሉ። ትምህርት ቤቶቹ እንደ ተማሪው ዜግነት፣ የክፍል ደረጃ እና የክፍያ ዓይነት የተለያየ ተመንም አላቸው።
አጃኢብ!
እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚወጣባቸው ግዙፍ የሽምግልና አበባዎች ፡ የአበባ አብዮት ወይስ የባህል ለውጥ?
ከጋብቻ በፊት የሚደረገው የሽምግልና ሥነ ሥርዓት ከፍተኛ ድግስ እና ገንዘብ የሚፈስበት እየሆነ መጥቷል። ከሚዘጋጀው ድል ያለ ድግስ ባሻገር በመቶ ሺዎች ብር የሚያስወጡ ቄንጠኛ ግዙፍ የአበባ ‘እቅፎች’ ደግሞ የሽምግልናው ሥርዓት አካል ሆነዋል። በተለይ የሚቀርበው የአበባ ስጦታ መነጋገሪያ ሆኗል። የሽምግልና ሥነ ሥርዓት የሰርግን ቦታ እየተካ ነው? ግዙፉ የአበባ ስጦታስ ከየት የመጣ ልማድ ነው?
የተመለሱ ጥያቄዎች
የአዲስ ዓመት አከባበር ሥርዓቶች በተለያዩ የዓለም አገራት
በዓለም ላይ ያሉ የተለያዩ አገራት ሕዝቦች አዲስ ዓመታቸውን የሚያከብሩት በተለያየ ጊዜ ነው። በርካታ የምዕራባውያን እና ከእነሱ ጋር ትስስር ያላቸው አገራት ጥር ወር ላይ አዲስ ዓመታቸውን የሚጀምሩ ሲሆን፣ አንዳንድ የእስያ አገራት ደግሞ ከዚህ የተለየ የአዲስ ዓመት አከባበር አላቸው። በተለያዩ የዓለማችን ክፍል የሚገኙ አገራት አዲስ ኣመትን እንዴት ያከብሩታል?
ቪዲዮ, ባለፓስፖርቶቹ የሰውን በሽታ የሚለዩት አይጦች, ርዝመት 1,28
ባለፓስፖርቶቹ የሰውን በሽታ የሚለዩት አይጦች
ቪዲዮ, የቦዲ ቢዩልደሮችን ልብ ቀጥ እያደረገ ያለው ነገር ምንድን ነው?, ርዝመት 1,24
የቦዲ ቢዩልደሮችን ልብ ቀጥ እያደረገ ያለው ነገር ምንድን ነው?